35 እረኞች የሚሸሹበት፣የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም።
36 እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቶአልና፣የእረኞችን ጩኸት፣የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ።
37 ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ሰላማዊው ምድር ባድማ ይሆናል።
38 እንደ አንበሳ ከጐሬው ይወጣል፤ከአስጨናቂው ሰይፍ፣ከቍጣውም የተነሣ፣ምድራቸው ባድማ ትሆናለች።