1 “በዚያ ዘመን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለእስራኤል ነገድ ሁሉ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”
2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።”
3 እግዚአብሔር ከሩቅ ተገለጠልን፤ እንዲህም አለን፤“በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ።
4 የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና አንጽሻለሁ፤አንቺም ትታነጪያለሽ፤ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣ከሚፈነጥዙት ጋር ትፈነድቂያለሽ።
5 እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣ወይን ትተክያለሽ፤አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤በፍሬውም ደስ ይላቸዋል።