14 “ ‘ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል እግዚአብሔር።
15 “ ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ፣ከዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ አበቅላለሁ፤በምድሪቱም ፍትሕንና ጽድቅን ያደርጋል።
16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች፤የምትጠራበትም ስም፣“እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።’
17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ከዳዊት ዘር በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤
18 ሌዋውያን ከሆኑት ካህናትም የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ፣ የእህል ቍርባን ለማቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ለመሠዋት ሁል ጊዜ በፊቴ የሚቆም ሰው አይታጣም።’ ”
19 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
20 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለቀንና ለሌሊት የወሰንሁትን ሥርዐት በማፋለስ ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣