11 በዚያን ጊዜ፣ ለእዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን፣ ከዚያ የበረታ የሚጠብስ ደረቅ ነፋስ በምድረ በዳ ካሉት ባድማ ኰረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ
12 በእኔ ትእዛዝ ይነፍሳል፤ እንግዲህ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።”
13 እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤መጥፋታችን ነውና ወዮልን!
14 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እንድትድኚ ከልብሽ ክፋት ታጠቢ፤እስከ መቼ ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ ይኖራል?
15 ድምፅ ከዳን ይሰማልና፤ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።
16 “ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤‘ከበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤
17 ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ”ይላል እግዚአብሔር።