1 ስለ ሕዝቦች ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
2 ስለ ግብፅ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ በከርከሚሽ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ባሸነፈው በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ኒካዑ ሰራዊት ላይ የተነገረ መልእክት ይህ ነው፤
3 “ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ለውጊያም ውጡ
4 ፈረሶችን ጫኑ፤በላያቸውም ተቀመጡ፤የራስ ቍር ደፍታችሁ፣በየቦታችሁ ቁሙ፤ጦራችሁን ወልውሉ፤ጥሩራችሁን ልበሱ