ኤርምያስ 48:33-39 NASV

33 ከሞዓብ የአትክልት ቦታና እርሻ፣ሐሤትና ደስታ ርቆአል፤የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣የእልልታ ድምፅ አይደለም።

34 “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35 በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

36 “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል።ያከማቹት ንብረት ጠፍቶአልና።

37 የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

38 በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፤፣በሕዝብም አደባባዮች፣ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤እንደማይፈለግ እንስራ፣ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።

39 “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ!ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ!ሞዓብ የመሰደቢያ፣በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”