ኤርምያስ 50:17-23 NASV

17 “እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣የተበተነ መንጋ ነው፤መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ቦጫጭቆ በላው፤በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣አጥንቱን ቈረጣጠመው።”

18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁት ሁሉ፣የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።

19 እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤በቀርሜሎስና በባሳን ላይ ይሰማራል፤በኤፍሬም ተራሮችና በገለዓድም ላይ፣እስኪጠግብ ይመገባል።

20 በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣”ይላል እግዚአብሔር፤“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤አንዳችም አይገኝም፤የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤ከቶም የለም፤እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ትሩፋን እምራለሁና።

21 “የምራታይምን ምድር፣የፋቁድ ነዋሪዎችንም፣አሳዷቸው፤ ግደሏቸው፤ ፈጽማችሁም አጥፏቸው፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ።

22 በምድሪቱ የጦርነት ውካታ፣የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰማ።

23 የምድር ሁሉ መዶሻ፣እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ!በሕዝቦች መካከል፣ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች!