21 “የምራታይምን ምድር፣የፋቁድ ነዋሪዎችንም፣አሳዷቸው፤ ግደሏቸው፤ ፈጽማችሁም አጥፏቸው፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ።
22 በምድሪቱ የጦርነት ውካታ፣የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰማ።
23 የምድር ሁሉ መዶሻ፣እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ!በሕዝቦች መካከል፣ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች!
24 ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ተገኘሽ፤ ተያዝሽም።
25 እግዚአብሔር የመሣሪያ ግምጃ ቤቱን ከፍቶአል፤የቍጣውን የጦር ዕቃ አውጥቶአል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በባቢሎናውያን ምድር ሥራ አለውና።
26 ከሩቅ መጥታችሁ በእርሷ ላይ ውጡ፤ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ፈጽማችሁ አጥፏት፤ምኗም አይቅር።
27 ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ወደ መታረጃም ይውረዱ!የሚቀጡበት ጊዜ፣ቀናቸው ደርሶአልና ወዮላቸው!