ኤርምያስ 6:19-25 NASV

19 ምድር ሆይ፤ ስሚ፤ቃሌን ስላላደመጡ፣ሕጌንም ስለናቁ፣በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ውጤት፣ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ።

20 ዕጣን ከሳባ ምድር፣ጣፋጩ ቅመም ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል?የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም፤

21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክልን አስቀምጣለሁ፤አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድነት ይደናቀፉበታል፤ጎረቤቶችና ባልንጀሮችም ይጠፋሉ።”

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ ሰራዊት፣ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ከምድር ዳርቻም፣ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

23 ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፤ድምፃቸው እንደተናወጠ ባሕር ነው፤የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ሊወጉሽ ይመጣሉ።”

24 ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥምሴት ሆነናል።

25 ጠላት ሰይፍ ታጥቆአል፤በየቦታውም ሽብር ሞልቶአል፤ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤በየመንገዱ አትዘዋወሩ።