ኤርምያስ 9:10-16 NASV

10 ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች አዝናለሁ፤ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።

11 “ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣የቀበሮም ጐሬ አደርጋታለሁ፤የይሁዳንም ከተሞች፣ሰው የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”

12 ይህን መረዳት የሚችል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? እግዚአብሔር ገልጾለት ይህንስ ማስረዳት የሚችል ማን ነው? ምድሪቱስ ሰው እንደማያልፍበት በረሓ ለምን ጠፋች? ለምን ወና ሆነች?

13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው።

14 በዚህ ፈንታ፣ በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን በአሊምን ተከተሉ።”

15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ።

16 እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን በማያውቋቸው ሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”