21 የሚሸሸው ወታደሩ ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል፤ የተረፉትም ወደ ነፋስ ይበተናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።
22 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከረጅሙ ዝግባ ጫፍ እኔው ራሴ ቀንበጡን ወስጄ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹ ጫፍ አንዱን ቀንጥሼ ከሁሉ ከፍ ባለው ተራራ ላይ እተክለዋለሁ።
23 ከፍ ባለው የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎች ያወጣል፤ ፍሬ ያፈራል፤ ያማረም ዝግባ ይሆናል። የወፍ ዐይነት ሁሉ መኖሪያውን በዚያ ያደርጋል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ያርፋል።
24 የዱር ዛፎች ሁሉ ረጅሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ።”“ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”