6 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤“ ‘ለዛገችው ብረት ድስትዝገቷም ለማይለቅ፣ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!መለያ ዕጣ ሳትጥልአንድ በአንድ አውጥተህ ባዶ አድርገው።
7 “ ‘የሰው ደም በመካከሏ አለ፤በገላጣ ዐለት ላይ አደረገችው እንጂ፣ዐፈር ሊሸፍነው በሚችል፣በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
8 ቍጣዬ እንዲነድና ለመበቀል እንዲያመቸኝ፣ይሸፈንም ዘንድ እንዳይችል፣ደሟን በገላጣ ዐለት ላይ አፈሰስሁ።
9 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።
10 ማገዶውን ከምርበት፤እሳቱን አንድድ፤ቅመም ጨምረህበት፣ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ዐጥንቱም ይረር።
11 ጒድፉ እንዲቀልጥ፣ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው።
12 ብዙ ጒልበት ቢፈስበትም፣የዝገቱ ክምር፣በእሳት እንኳ፣ ሊለቅ አልቻለም።