1 እናንት ደሴቶች ስሙኝ፤እናንት በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።
2 አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ።
3 እርሱም፣ “እስራኤል፤ አንተ ባሪያዬ ነህ፤በአንተ ክብሬን እገልጣለሁ” አለኝ።
4 እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጒልበቴን ጨረስሁ፤ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ።
5 በእግዚአብሔር ዐይን ፊት ከብሬአለሁ፤አምላኬ ጒልበት ሆኖልኛል፤ባሪያው እንድሆን ከማሕፀን የሠራኝ፣ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፣እስራኤልን ወደ እርሱ እንድሰበስብ ያደረገኝ፣ እግዚአብሔር አሁንም እንዲህ ይላል፤
6 እርሱም፣“ባሪያዬ መሆንህ፣የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።