5 “ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ’
6 ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ከሰሜን መቅሠፍትን፣ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”
7 አንበሳ ከደኑ ወጥቶአል፤ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቶአል፤ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ከስፍራው ወጥቶአል።ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።
8 ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤እዘኑ፤ ዋይ በሉ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ፣ከእኛ አልተመለሰምና።
9 ‘ “በዚያ ቀን” ይላል እግዚአብሔር፤“ንጉሡና ሹማምቱ ወኔ ይከዳቸዋል፤ካህናቱ ድንጋጤ ይውጣቸዋል፤ነቢያቱም ብርክ ይይዛቸዋል።”
10 እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰይፍ አንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።
11 በዚያን ጊዜ፣ ለእዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን፣ ከዚያ የበረታ የሚጠብስ ደረቅ ነፋስ በምድረ በዳ ካሉት ባድማ ኰረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ