1 ስለ ሞዓብ፤የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።
2 ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል።መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ሰይፍም ያሳድድሻል።
3 ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!
4 ሞዓብ ትሰበራለች፤ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።
5 ክፉኛ እያለቀሱ፣ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።
6 ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ!በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ።