12 የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
13 ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።
14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ርትዕ አሰፈነላቸው።
16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።
17 እንዲሁም የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሓፊ ነበረ፤
18 የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የቤተ መንግሥት አማካሪዎች ነበሩ።