2 ንጉሡ ዮአኪን በተማረከ በአምስተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ቀን፣
3 በባቢሎናውያን ምድር በኮቦር ወንዝ አጠገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቡዝ ልጅ፣ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ በዚያ የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረች።
4 እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር።
5 በእሳቱም ውስጥ የአራት ሕያዋን ፍጡራን አምሳያ ነበረ፤ መልካቸውም የሰው ቅርጽ ይመስል ነበር።
6 እያንዳንዳቸውም አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው።
7 እግራቸው ቀጥ ያለ ነበር፤ ኮቴያቸውም እንደ ጥጃ ኮቴ ያለ ሲሆን፣ እንደ ተወለወለ ናስም ያበለጨልጭ ነበር።
8 በአራቱ ጐኖቻቸው ባሉት ክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ ነበራቸው። አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው፤