1 በዘጠነኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በዐሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ቀን፣ የዛሬውን ዕለት ለይተህ መዝግብ፤ የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በዚህ ቀን ከቦአታልና።
3 ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ ብለህ ተምሳሌት ተናገር፤ ‘ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ብረት ድስት በእሳት ላይ ጣድ፤ከጣድህም በኋላ ውሃ ጨምርበት።
4 ሙዳ፣ ሙዳ ሥጋ፣ምርጥ ምርጡን ቍርጥ ሁሉ፣ ጭንና ወርቹን ጨምርበት፤የተመረጡ ዐጥንቶችንም ሙላበት።
5 ከመንጋው ሙክቱን ውሰድ፤ዐጥንቱን ለማብሰል ብዙ ማገዶ ከሥሩ ጨምር፤ሙክክ እስከሚል ቀቅለው፤ዐጥንቱም ይብሰል።
6 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤“ ‘ለዛገችው ብረት ድስትዝገቷም ለማይለቅ፣ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!መለያ ዕጣ ሳትጥልአንድ በአንድ አውጥተህ ባዶ አድርገው።
7 “ ‘የሰው ደም በመካከሏ አለ፤በገላጣ ዐለት ላይ አደረገችው እንጂ፣ዐፈር ሊሸፍነው በሚችል፣በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።