3 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ።
4 የጢሮስን ቅጥሮች ያወድማሉ፤ ምሽጎቿንም ያፈርሳሉ። ዐፈሯን ከላይዋ ጠርጌ የተራቈተ ዐለት አደርጋታለሁ።
5 እኔ ልዑል እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፤ በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች፤ አሕዛብም ይበዘብዟታል፤
6 መኻል አገር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይወድማሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።
7 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋር፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋር ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
8 እርሱ መኻል አገር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማቸዋል፤ በዙሪያሽ ካብ ይክባል፤ እስከ ቅጥሮችሽ ጫፍ ድረስ ዐፈር ይደለድ ልብሻል፤ ጋሻውንም በአንቺ ላይ ያነሣል።
9 ግንብ መደርመሻውን በቅጥሮቿ ላይ ያነጣጥራል፤ በመሣሪያም ምሽጎችሽን ያፈርሳል።