ሕዝቅኤል 30:3-9 NASV

3 ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤የደመና ቀን፣ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።

4 በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ይወሰዳል፤መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።

5 ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።

6 “ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።ከሚግዶል እስከ አስዋን፣በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

7 “ ‘በባድማ መሬቶች መካከል፣ባድማ ይሆናሉ፤ከተሞቻቸውም፣ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።

8 በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቁ፣በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ፤

9 “ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።