ሕዝቅኤል 30:5-11 NASV

5 ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።

6 “ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።ከሚግዶል እስከ አስዋን፣በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

7 “ ‘በባድማ መሬቶች መካከል፣ባድማ ይሆናሉ፤ከተሞቻቸውም፣ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።

8 በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቁ፣በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ፤

9 “ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።

10 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብፅን ሕዝብ እደመስሳለሁ።

11 ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ሰይፋቸውን በግብፅ ላይ ይመዛሉ፤ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤