ሕዝቅኤል 41:10-16 NASV

10 በካህናቱ ክፍሎች መካከል ያለ ሲሆን፣ ስፋቱ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሃያ ክንድ ነበር።

11 ከክፍቱ ቦታ ግራና ቀኝ ወዳሉ ክፍሎች የሚያስገቡ በሮች ነበሩ። አንዱ በሰሜን በኩል ሲሆን፣ ሌላው በር ደግሞ በደቡብ በኩል ነው። ክፍቱን ቦታ ዙሪያውን የሚያገናኘው መሠረት ስፋቱ አምስት ክንድ ነው።

12 በምዕራብ በኩል ከቤተ መቅደሱ ግቢ ትይዩ የሆነው ሕንጻ ወርድ ሰባ ክንድ ነበር። የሕንጻው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን አምስት ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዘጠና ክንድ ነበር።

13 ከዚያም ቤተ መቅደሱን ለካ፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ የቤተ መቅደሱ ግቢና ሕንጻ ከነግንቡ ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።

14 በምሥራቅ በኩል የቤተ መቅደሱ ግቢ ስፋት፣ ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን ስፍራ ጨምሮ አንድ መቶ ክንድ ነበር።

15 ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተ ጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር።የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣

16 እንዲሁም መድረኮቹና ጠበብ ያሉት መስኮቶች፣ በሦስቱም ዙሪያ ያሉት መተላለፊያዎች፣ ከመድረኩ በላይና ራሱ መድረኩም ጭምር ሁሉም በዕንጨት ተለብዶ ነበር። ወለሉ፣ እስከ መስኮቶቹ ያለው ግንብና መስኮቶቹ ተለብደዋል።