19 “በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብፅን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።
20 “በምዕራቡ በኩል ወሰኑ ከሐማት መግቢያ ፊት ለፊት እስካለው ቦታ ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል፤ ይህም የምዕራቡ ወሰን ይሆናል።
21 “እነሆ፤ ይህችን ምድር በእስራኤል ነገድ ቍጥር ልክ ትከፋፈላላችሁ፤
22 ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።
23 መጻተኛ በማንኛውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ፣ በዚያ ርስቱን ስጡት” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።