ሕዝቅኤል 48:27-33 NASV

27 “ ‘የጋድ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የዛብሎንን ግዛት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

28 “ ‘የጋድ ደቡባዊ ወሰን ከታማር ደቡብ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውሆች ይደርሳል፤ የግብፅን ደረቅ ወንዝ ይዞ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል።

29 “ ‘ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤ ድርሻዎቻቸውም እነዚህ ናቸው” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

30 “ ‘የከተማዪቱ መውጫ በሮች እነዚህ ናቸው፤ ከሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ካለው በር አንሥቶ፣

31 የከተማዪቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ያሉት ሦስቱ በሮች የሮቤል ነገድ በር፣ የይሁዳ ነገድ በርና የሌዊ ነገድ በር ይሆናሉ።

32 “ ‘በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የዮሴፍ በር፣ የብንያም በርና የዳን በር ናቸው።

33 “ ‘በደቡብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች አሉ፤ እነዚህም የስምዖን በር፣ የይሳኮር በርና የዛብሎን በር ናቸው።