ሕዝቅኤል 48:29-35 NASV

29 “ ‘ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤ ድርሻዎቻቸውም እነዚህ ናቸው” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

30 “ ‘የከተማዪቱ መውጫ በሮች እነዚህ ናቸው፤ ከሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ካለው በር አንሥቶ፣

31 የከተማዪቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ያሉት ሦስቱ በሮች የሮቤል ነገድ በር፣ የይሁዳ ነገድ በርና የሌዊ ነገድ በር ይሆናሉ።

32 “ ‘በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የዮሴፍ በር፣ የብንያም በርና የዳን በር ናቸው።

33 “ ‘በደቡብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች አሉ፤ እነዚህም የስምዖን በር፣ የይሳኮር በርና የዛብሎን በር ናቸው።

34 “ ‘በምዕራብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የጋድ በር፣ የአሴር በርና የንፍታሌም በር ናቸው።

35 “ ‘የከተማዪቱም ዙሪያ ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤“ ‘የከተማዪቱ ስም፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ “እግዚአብሔር በዚያ አለቃ ይሆናል።’ ”