3 ከድነቴ ምንጮችውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4 በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤“እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6 የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤በደስታም ዘምሩ፤በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።