ኢሳይያስ 16:2-8 NASV

2 ከጐጆአቸው ተባርረውግራ እንደ ተጋቡ ወፎች፣የሞዓብ ሴቶችምበአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ።

3 “ምክር ለግሱን፤ውሳኔ ስጡን፤በቀትር ጥላችሁንእንደ ሌሊት አጥሉብን፤የሸሹትን ደብቁ፤ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።

4 የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋር ይቈዩ፤እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።”የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ጥፋቱ ያከትማል፤እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።

5 ዙፋን በፍቅር ይመሠረታል፤ከዳዊት ቤት የሆነ፣በፍርድ ፍትሕን የሚሻ፣ጽድቅንም የሚያፋጥን፣አንድ ሰው በታማኝነት በላዩ ይቀመጣል።

6 የሞዓብን መዘባነን፣እጅግ መታበዩንና ኵራቱን፣እብሪቱንና ስድነቱን ሰምተናል፤ትምክህቱ ግን ከንቱ ነው።

7 ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣በሐዘን ያለቅሳሉ።

8 የሐሴቦን ዕርሻ፣የሴባማም የወይን ተክል ጠውልጎአል፤የአሕዛብ ገዦች፣ኢያዜርን ዐልፈው፣ምድረ በዳውን ዘልቀው፣ሥሮቻቸውን እስከ ባሕር ሰድደው የነበሩትንየተመረጡ የወይን ተክሎችንረጋግጠዋል።