ኢሳይያስ 27:5-11 NASV

5 አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠሩ፤አዎን፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።”

6 በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤እስራኤልም ያቈጠቍጣል፤ ያብባልም፤በፍሬያቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ።

7 የመቷትን እንደ መታቸው፣ እግዚአብሔር እርሷንስ መታትን?የገደሏትን እንደ ገደላቸው፣እርሷስ ተገደለችን?

8 በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።

9 ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቃቸው፣የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣በዚያን ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ይህም ኀጢአቱን የማስወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።

10 የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤እዚያም ይተኛሉ፤ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።

11 ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል።ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ፈጣሪው አይራራለትም፤ያበጀውም አይምረውም።