1 አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ! የፈጠረህ፤እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤
2 በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ወንዙን ስትሻገረው፣አያሰጥምህም፤በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣አያቃጥልህም፤ነበልባሉም አይፈጅህም።
3 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ግብፅን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።
4 ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣እኔም ስለምወድህ፣ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።
5 ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
6 ሰሜንን፣ ‘አምጣ’፣ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣