ኢሳይያስ 44:20-26 NASV

20 ዐመድ ይቅማል፤ ተታላይ ልብ አስቶታል፤ራሱን ለማዳን አይችልም፤“ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ሐሰት አይደለምን?”ለማለት አልቻለም።

21 “እስራኤል ሆይ፤ ባሪያዬ ነህና፣ያዕቆብ ሆይ፤ ይህን አስብ።እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤እስራኤል ሆይ፤ አልረሳህም።

22 መተላለፍህን እንደ ደመና፣ኀጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ ጠርጌ አስወግጃለሁ፤ተቤዥቼሃለሁናወደ እኔ ተመለስ።”

23 ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጎአልና ዘምሩ፤የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ።እናንት ተራሮች፣እናንት ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአል፣በእስራኤልም ክብሩን ገልጦአልና።

24 “ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ምድርን ያንጣለልሁ፣እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

25 የሐሰተኞችን ነቢያት ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ሟርተኞችን አነሆልላለሁ፤የጥበበኞችን ጥበብ እገለባብጣለሁ፤ዕውቀታቸውንም ከንቱ አደርጋለሁ።

26 የባሪያዎቼን ቃል እፈጽማለሁ፤የመልእክተኞቼን ምክር አጸናለሁ።ኢየሩሳሌምን ‘የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ’፣የይሁዳ ከተሞችንም፣ ‘ይታነጻሉ’፣ፍርስራሻቸውን፣ ‘አድሳለሁ’ እላለሁ።