3 ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።
4 “ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ሁሉም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ፣ሴቶች ልጆችሽም በዕቅፍ ወደ አንቺ ይመጣሉ።
5 ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂያለሽ፤ልብሽ ይዘላል፤ በደስታም ይሞላል።በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤የነገሥታትም ብልጥግና የአንቺ ይሆናል።
6 የግመል መንጋ፣የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎችምድርሽን ይሞላሉ፤ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።
7 የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል።እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ።
8 “ርግቦች ወደ ጐጆአቸው እንደሚበሩ፣እንደ ደመና የሚጓዙ እነዚህ እነማን ናቸው?
9 በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።