ኢሳይያስ 63:6-12 NASV

6 መንግሥታትን በቍጣዬ ረጋገጥሁ፤በመዓቴም አሰከርኋቸው፤ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ።”

7 የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ስለሚመሰገንበት ሥራው፣እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ።

8 እርሱም፣ “ርግጥ ነው፤ እነርሱ ሕዝቤ ናቸው፤የማይዋሹኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው” አለ።ስለዚህም አዳኝ ሆነላቸው።

9 በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ተሸከማቸውም።

10 እነርሱ ግን ዐመፁ፤ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ፤ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፤እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።

11 ከዚያም ሕዝቡ የጥንቱን ዘመን፣የሙሴንና የሕዝቡን ጊዜ እንዲህ በማለት አስታወሱ፤የበጎቹን እረኛ፣ከባሕሩ ያወጣቸው እርሱ የት አለ?ቅዱስ መንፈሱንም፣በመካከላቸው ያኖረ እርሱ የት አለ?

12 የከበረው ኀያል ክንድ፣በሙሴ ቀኝ እጅ ላይ እንዲያርፍ አደረገ፤ለራሱ የዘላለም ዝና እንዲሆንለት፣ውሆችን በፊታቸው ከፈለ።