ኤርምያስ 11:12-18 NASV

12 የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም።

13 ይሁዳ ሆይ፤ የአማልክትህ ቍጥር የከተሞችህን ብዛት ያህል ነው፤ አሳፋሪ ለሆነው ጣዖት፣ ለበኣል ማጠኛ የሠራችኋቸው መሠዊያዎቻችሁ ብዛት የኢየሩሳሌምን መንገዶች ያህል ነው።’ ”

14 “በተጨነቁ ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ልመና አታቅርብ፤ አትማጠን።

15 “ወዳጄ፣ ከብዙዎች ጋር ተንኰሏን እየሸረበች፣በቤቴ ውስጥ ምን ጒዳይ አላት?ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ሊያስቀርልሽ ይችላልን?እነዚህንስ በመፈጸም፣ ደስተኛ መሆንትችያለሽን?”

16 እግዚአብሔር፣ ‘የተዋበ ፍሬ ያላት፣የለመለመች የወይራ ዛፍ’ ብሎሽ ነበር፤አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣እሳት ያነድባታል፤ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ።

17 የእስራኤልና የያዕቆብ ቤት ለበኣል በማጠን ባደረጉት ክፋት ስላስቈጡኝ፣ አንቺን የተከለሽ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉ ነገር ዐውጆብሻል።

18 እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያን ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና።