ኤርምያስ 12:1-7 NASV

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጒዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው።የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?

2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰደዋል፤አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል።ሁል ጊዜ አንተ በአፋቸው ላይ አለህ፤ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

3 ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ።እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤

4 ምድሪቱ በዝናብ እጦት የምትጐዳው፣የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው?ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ደግሞም ሕዝቡ፣“በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።

5 “ከእግረኞች ጋር ሮጠህ፣እነርሱ ካደከሙህ፣ከፈረሰኞች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

6 ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤በመልካም ቢናገሩህም እንኳአትመናቸው።

7 “ቤቴን እተዋለሁ፤ርስቴን እጥላለሁ፤የምወዳትን እርሷን፣አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ።