ኤርምያስ 12:4-10 NASV

4 ምድሪቱ በዝናብ እጦት የምትጐዳው፣የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው?ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ደግሞም ሕዝቡ፣“በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።

5 “ከእግረኞች ጋር ሮጠህ፣እነርሱ ካደከሙህ፣ከፈረሰኞች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

6 ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤በመልካም ቢናገሩህም እንኳአትመናቸው።

7 “ቤቴን እተዋለሁ፤ርስቴን እጥላለሁ፤የምወዳትን እርሷን፣አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ።

8 ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳተነሥታብኛለችበእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ስለዚህ ጠላኋት።

9 ርስቴ ሌሎች አሞሮች፣ሊበሏት እንደ ከበቧት፣እንደ ዝንጒርጒር አሞራ አልሆነችምን?ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤እንዲቀራመቷትም አምጧቸው።

10 ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።