3 መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤እነርሱ ወደ ውሃ ጒድጓዶች ይወርዳሉ፤ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ራሳቸውን ተከናንበው፣ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።
4 በምድሪቱ ዝናብ ስለሌለ፣መሬቱ ተሰነጣጥቆአል፤ገበሬዎችም ዐፍረው፣ራሳቸውን ተከናንበዋል።
5 አንዳች ሣር ባለመኖሩ፣የሜዳ አጋዘን እንኳ፣እንደ ወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።
6 የሜዳ አህዮች ባድማ ኰረብቶች ላይ ቆሙ፤እንደ ቀበሮም አየር ፍለጋ አለከለኩ፤ግጦሽ ባለመገኘቱ፣ዐይኖቻቸው ፈዘዙ።”
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።
8 አንተ የእስራኤል ተስፋ፤በጭንቀት ጊዜ አዳኙ፣ለምን በምድሪቱ እንደ ባዕድ፣እንደ ሌት አዳሪ መንገደኛ ትሆናለህ?
9 ግራ እንደ ተጋባ ሰው፣ለመታደግም ኀይል እንዳጣ ተዋጊ ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመካከላችን አለህ፤በስምህም ተጠርተናል፤እባክህ አትተወን።