12 የመቅደሳችን ስፍራ፣ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።
13 የእስራኤል ተስፋ እግዚአብሔር ሆይ፤ጥለውህ የሚሄዱ ሁሉ ያፍራሉ፤ፊታቸውን ከአንተ የሚመልሱ በምድር ውስጥ ይጻፋሉ፤የሕይወትን ውሃ ምንጭ፣ እግዚአብሔርን ትተዋልና።
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈውሰኝ፤ እፈወሳለሁ፤አድነኝ እኔም እድናለሁ፤አንተ ምስጋናዬ ነህና።
15 እነርሱ ደጋግመው፣“የእግዚአብሔር ቃል የት አለ?እስቲ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።
16 እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።
17 አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤በመከራ ቀን መሸሸጊያዬ አንተ ነህ።
18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፤እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤እነርሱ ይደንግጡ፤እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ክፉ ቀን አምጣባቸው፤በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።