ኤርምያስ 20:2-8 NASV

2 ነቢዩ ኤርምያስን መታው፣ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።

3 በማግስቱም ጳስኮር ኤርምያስን ከተጠረቀበት ግንድ አወጣው፤ ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ከእንግዲህ ማጎርሚሳቢብ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም፤

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ባልንጀሮችህን ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።

5 የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ።

6 ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ባልንጆሮችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ሁሉም ተዘባበቱብኝ።

8 በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤“ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ።