17 እኔን ለሚንቁኝ፣‘እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል’ ይላሉ፤የልባቸውን እልኸኝነት ለሚከተሉም ሁሉ፣‘ክፉ ነገር አይነካችሁም’ ይሏቸዋል።
18 ቃሉን ለማየትና ለመስማት፣እነማን የእግዚአብሔር ምክር ባለበት ቆመዋል?ቃሉን ያደመጠ፣ የሰማስ ማን ነው?
19 እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣በቍጣ ይነሣል፤ብርቱም ማዕበል፣የክፉዎችን ራስ ይመታል።
20 እግዚአብሔር የልቡን ሐሳብ፣ሙሉ በሙሉ ሳይፈጽም፣ቍጣው እንዲሁ አይመለስም፤በኋለኛው ዘመን፣ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ።
21 እኔ እነዚህን ነቢያት አልላክኋቸውም፤እነርሱ ግን ለራሳቸው መልእክታቸውን ይዘው ሮጡ፣ሳልናገራቸውም፣ትንቢት ተናገሩ።
22 ምክሬ ባለበት ቢቆሙ ኖሮ፣ቃሌን ለሕዝቤ ባሰሙ ነበር፤ከክፉ መንገዳቸው፣ከክፉ ሥራቸውም በመለሷቸው ነበር።
23 “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝን?ይላል እግዚአብሔር፤“የሩቅስ አምላክ አይደለሁምን?