2 “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።
3 እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”
4 እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
5 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቶአል፤ሰላምም የለም።
6 እስቲ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ወንድ መውለድ ይችላል?ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?
7 ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል!እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ነገር ግን ይተርፋል።
8 “ ‘በዚያን ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዙአቸውም።