ኤርምያስ 31:12-18 NASV

12 መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ከእንግዲህም አያዝኑም።

13 ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤ልቅሶአቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ።

14 ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤”ይላል እግዚአብሔር።

15 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ዋይታና መራራ ልቅሶ፣ከራማ ተሰማ፤ልጆቿ የሉምና፣ራሔል አለቀሰች፤መጽናናትም እንቢ አለች።”

16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ድምፅሽን ከልቅሶ፣ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክይ፤ድካምሽ ያለ ዋጋ አይቀርምና፤”ይላል እግዚአብሔር።“ከጠላት ምድር ይመለሳሉ፤

17 ስለዚህ ወደ ፊት ተስፋ አለሽ”ይላል እግዚአብሔር።“ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።

18 “የኤፍሬምን የሲቃ እንጒርጒሮ በእርግጥ ሰምቻለሁ፤‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤እኔም ተቀጣሁ።አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።