2 ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል።መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ሰይፍም ያሳድድሻል።
3 ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!
4 ሞዓብ ትሰበራለች፤ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።
5 ክፉኛ እያለቀሱ፣ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።
6 ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ!በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ።
7 በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣እናንተም ትማረካላችሁ፣ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣በምርኮ ይወሰዳል።
8 በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና፣ሸለቆው ይጠፋል፤ዐምባውም ይፈርሳል።