37 የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።
38 በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፤፣በሕዝብም አደባባዮች፣ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤እንደማይፈለግ እንስራ፣ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።
39 “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ!ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ!ሞዓብ የመሰደቢያ፣በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”
40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።
41 ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቹም ይያዛሉ፤በዚያን ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።
42 ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሎአልና ይጠፋል፤መንግሥትነቱም ይቀራል።
43 የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤ሽብርና ጒድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤”ይላል እግዚአብሔር።