ኤርምያስ 50:26-32 NASV

26 ከሩቅ መጥታችሁ በእርሷ ላይ ውጡ፤ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ፈጽማችሁ አጥፏት፤ምኗም አይቅር።

27 ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ወደ መታረጃም ይውረዱ!የሚቀጡበት ጊዜ፣ቀናቸው ደርሶአልና ወዮላቸው!

28 እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።

29 “ቀስት የሚገትሩትን፣ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤የእስራኤልን ቅዱስ፣ እግዚአብሔርን አቃላለችና፣እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።

30 ስለዚህ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

31 “አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፣ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤“የምትቀጣበት ጊዜ፣ቀንህ ደርሶአልና።

32 ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤የሚያነሣውም የለም፤በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።”