ኤርምያስ 50:38-44 NASV

38 ድርቅ በውሆቿ ላይ መጣ!እነሆ፤ ይደርቃሉ፤ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።

39 “ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣የጒጒትም ማደሪያ ትሆናለች፤ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።

40 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፤በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀራቸው”ይላል እግዚአብሔር፤“እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፣የሚቀመጥባትም አይገኝም።

41 “እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።

42 ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተማል፤ ያስገመግማል።አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።

43 የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤እጆቹም በድን ሆኑ፤ጭንቀት ይዞታል፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታሟል።

44 አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤የመረጥሁትንም በእርሷ ላይ እሾማለሁ፤እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል?የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?