1 “እናንት የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍአድርጋችሁ አሳዩ።
2 ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ።
3 እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።”
4 “በእርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤ወይ ጉድ! ቀኑ እኮ መሸብን!ጥላው ረዘመ።