1 “ ‘በዚያን ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንት ዐፅም፣ የካህናትና የነቢያት ዐፅም፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዐፅም ከየመቃብራቸው ይወጣል።
2 በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደተጣለ ጒድፍ በምድር ላይ ይበተናል።
3 ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’
4 “እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን?ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን?