1 ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ!ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጒረፊያ በሆኑልኝ!
2 ሕዝቤን ትቼ፣ ርቄ እንድሄድ፣በምድረ በዳ የእንግዶች ማደሪያ ማን በሰጠኝ!ሁሉም አመንዝሮች፣የአታላዮች መንጋ ሆነዋላ!
3 “ሐሰትን ለመናገር፣ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤በእውነት ሳይሆን፣በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤እኔንም አላወቁኝም፤”ይላል እግዚአብሔር።
4 “እያንዳንዱ ወንድም አታላይ፣ባልንጀራም ሁሉ ሐሜተኛ ስለ ሆነ፣ወንድም ከወንድሙ፣ ይጠንቀቅ፣ባልንጀራም በጓደኛው አይታመን።