ኤርምያስ 9:16-22 NASV

16 እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን በማያውቋቸው ሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”

17 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እንግዲህ፤ አልቃሽ ሴቶች ጥሩ፤ሥልጡን ሙሾ አውራጆች አስመጡ፤

18 እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን።

19 እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቶአል፤ እንዲህም ይላል፤‘ምንኛ ወደቅን!ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው!ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”

20 እናንት ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።

21 ሞት በመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቆአል፤ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዶአል።

22 እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የሰዎች ሬሳ፣በሜዳ እንደተጣለ ጒድፍ፣ማንም እንደማይሰበስበው፣ከዐጫጅ ኋላ እንደተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”