ኤርምያስ 9:2-8 NASV

2 ሕዝቤን ትቼ፣ ርቄ እንድሄድ፣በምድረ በዳ የእንግዶች ማደሪያ ማን በሰጠኝ!ሁሉም አመንዝሮች፣የአታላዮች መንጋ ሆነዋላ!

3 “ሐሰትን ለመናገር፣ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤በእውነት ሳይሆን፣በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤እኔንም አላወቁኝም፤”ይላል እግዚአብሔር።

4 “እያንዳንዱ ወንድም አታላይ፣ባልንጀራም ሁሉ ሐሜተኛ ስለ ሆነ፣ወንድም ከወንድሙ፣ ይጠንቀቅ፣ባልንጀራም በጓደኛው አይታመን።

5 ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤እውነትን የሚናገር የለም፤ሐሰትን ይናገር ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።

6 መኖሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፤ከሽንገላቸውም የተነሣ ሊያውቁኝ አልፈቀዱም፤”ይላል እግዚአብሔር።

7 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?

8 ምላሳቸው የሚገድል ቀስት ነው፤በሽንገላ ይናገራል፤ሁሉም ከባልንጀራው ጋር በፍቅር ይናገራል፤በልቡ ግን ያደባበታል።